🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፡-በየም ዞን የሚገኙ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ የመስህብ ስፍራዎችን በማልማት የቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ በርካታ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን በማልማት የቱሪዝም ዘርፍን ለማነቃቃት ባለፉት ዓመታት ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል።

በሀገሪቱ በርካታ የሆኑ ግዙፍ የቱሪዝም ፕሮጀክቶች ግንባታ መጀመሩን እንዲሁም የተጀመሩት መጠናቀቃቸው ሀገሪቱ በዘርፉ ያላትን ዕምቅ አቅም አውጥቶ ለመጠቀም የሚያስችል ነው።
20ኛው የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ ከሀገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች በየም ዞኑ የሚገኙትን የዞፍካር ትክል ድንጋይ፤ የአንገሪ ቤተ-መንግስት፣ የብርብርሳ ፏፏቴ እና የቦር ተራራን ጎብኝተዋል።
የየም ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ መስፍን ሞጋ በዞኑ በርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ቅርሶች እንዳሉ ጠቅሰው፤ የመዳረሻ ስፍራዎችን በስፋት በማስተዋወቅ የጎብኝዎች ቁጥር እንዲጨምር ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

እነዚህን የቱሪዝም መዳረሻ ሀብቶችን በማልማት የቱሪዝም ዘርፍን ለማነቃቃት በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።
የቱሪዝም ዘርፉ ልማት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይና የሁሉንም ቅንጅታዊ አሰራር የሚፈልግ መሆኑን አንስተዋል።
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025