🔇Unmute
ጭሮ ፤ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፡- በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከ9 ሺህ 800 ቶን በላይ ጥራቱን የጠበቀ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ንግድ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ተወካይ አቶ ቃሲም ጀማል ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዞኑ ከ130 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ከለማ ቡና ከ9 ሺህ 800 ቶን በላይ ጥራቱን የጠበቀ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ነው።
በቡና ልማቱ ለተሳተፉ አርሶ አደሮችም ጥራት ያለው የቡና ምርትን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በዓመቱ ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የታቀደው የቡና ምርትም ባለፈው ዓመት ከነበረው ከ1 ሺህ ቶን በላይ ብልጫ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል፡፡
ጥራቱን በማስጠበቅና የምርት አያያዝና ህጋዊ ግብይትን በማስፈን ረገድ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማሳደግ መሰራቱን አመልክተዋል፡፡
የቡና ጥራትን ለማረጋገጥ ቀይ እሸት ቡናን በመልቀምና በአልጋ ላይ በማድረቅ በገበያ ተወዳዳሪ መሆን የሚቻልበት አሰራር መዘርጋቱን ተናግረዋል።
ጥራቱን የጠበቀ የቡና ምርት ለማእከላዊ ገበያ ለማቅረብም 132 ነጋዴዎች እና ሁለት ዩኒየኖች ፈቃድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።
ዩኒየኖቹ እና ነጋዴዎቹ በ35 የደረቅ ቡና መፈልፈያ ኢንዱስትሪዎች ምርቱን አዘጋጅተው ለገበያ እንደሚያቀርቡም ነው ያመለከቱት፡፡
የቡርቃ ጋሌይቲ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ ሶፊያን አህመድ እንዳሉት፤ በዩኒየኑ ስር ያሉ ማህበራት የቡና ጥራትን ለማረጋገጥ ከለቀማ እስከ ግብይት ባለው ሂደት ለጥራት ትኩረት እንዲሰጡ ግንዛቤ ተሰጥቷል።

ዩኒየኑ ጥራቱን የጠበቀ ቡና ከአባላቱ በማሰባሰብ ለገበያ በማቅረብ የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት የቡናና ቅመማ ቅመም ልማት ቡድን መሪ አቶ ኦሉማ በዳኔ በበኩላቸው፤ አርሶ አደሮች የደረሰ ቀይ ቡና ብቻ በመልቀም ጥራት ባለው የምርት መያዣ ለገበያ እንዲያቀርቡ የግብርና ባለሙያዎች ድጋፍ እያደረጉላቸው ነው ብለዋል፡፡
በዞኑ በየዓመቱ ለአርሶ አደሩ የሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና ድጋፍ ለገበያ የሚቀርበውን ቡና ምርት ጥራትና ብዛት እንዲጨምር አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የሲሚንቶ ንግድ እና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎች ገበያውን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመቀ...
Feb 12, 2025