🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 10/2018(ኢዜአ)፦አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአራብሳ አካባቢ የተገነባውን የንጹህ መጠጥ ውሃ መሠረተ ልማትና የኮዬ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
ከንቲባዋ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ፕሮጀክቱ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን በጉልህ እንደሚያሳድግ ገልጸዋል።

ባለፉት ዓመታት የመጠጥ ውሃ እጥረትን ለመፍታት የተከናወኑ ሥራዎች ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን ጠቅሰው፣የመዲናዋ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በቀን ከ910 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ መድረሱን አስታውቀዋል።
በቀጣይም ከፍተኛ የማምረት አቅም ያላቸው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ እንደሚገቡ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የኮዬ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የሕብረተሰቡን ጤናና የአካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ከንቲባዋ ገልጸዋል።
ጣቢያው ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም መሆኑን በማንሳት፣ መሰል የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎችን በስፋት ለመገንባት መታቀዱን አስረድተዋል።
መሠረተ ልማት መገንባት ብቻውን ግብ አይደለም ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ የተገነቡትን መሠረተ ልማቶች መጠበቅና መንከባከብ የሁሉም የጋራ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪና ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለማድረግ የተጀመሩት የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በማንሳት፣ ለፕሮጀክቶቹ እውን መሆን አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።
ሚዛን አማን፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በ2018 በጀት ዓመት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ...
Aug 14, 2026
ሮቤ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን በማልማትና በመጠበቅ ዘላቂ የገቢ ምንጭ ለማድረግ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ዱር...
Aug 7, 2026
ወልቂጤ ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በጉራጌ ዞን የመኸር አዝመራን ውጤታማ ለማድረግ ለሰብል እንክብካቤ፣ ለኩታገጠም እርሻና ለግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትኩ...
Jul 23, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 14/2018(ኢዜአ)፦ የተፈጥሮ ሀብትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ሥራዎች ለቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት ያላቸውን አስተዋጽኦ ይበልጥ የሚያጎሉ ተግባራት...
Jul 22, 2026