የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በዞኑ የመኸር አዝመራን ውጤታማ  ለማድረግ ለኩታ ገጠም እርሻና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትኩረት ተሰጥቷል

Jul 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወልቂጤ ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በጉራጌ ዞን የመኸር አዝመራን ውጤታማ ለማድረግ ለሰብል እንክብካቤ፣ ለኩታገጠም እርሻና ለግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትኩረት መሰጠቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ ፡፡

በዞኑ በአበሽጌ ወረዳ የኩታ ገጠም የመኸር አዝመራ ልማት የመስክ ምልከታ ተደርጓል፡፡


የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በወቅቱ እንደገለጹት፤ በዞኑ የመኸር ሰብልን ውጤታማ ለማድረግ በ177 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም የተለያዩ ሰብሎች ለምተዋል፡፡


በኩታ ገጠም እርሻውም በቆሎ፣ ማሽላ፣ ገብስ፣ አተር፣ ባቄላ፣ ሩዝ እና ጤፍ በኩታ ገጠም እየለማ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ለግብአት አቅርቦት፣ ለባለሙያ ድጋፍ፣ ለሰብል እንክብካቤና ለግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትኩረት ተሰጥቶ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡

የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሱ ጁሃር በበኩላቸው፤ በወረዳው በዘንድሮው የመኸር ወቅት ግብአትና የኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴን በመጠቀም አርሶ አደሮች ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡


የአበሽጌ ወረዳ የአቡኮ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ዘሪሁን ቱሉ፤ የግብርና ባለሙያዎች የሚያደርጉላቸውን ድጋፍ ተጠቅመው አራት ሄክታር ኩታ ገጠም መሬታቸውን በበቆሎ ማልማታቸውን ተናግረዋል።

የበቆሎ ሰብሉን ከአረም እና ከበሽታ በመከላከል የተሻለ ምርት ለማግኘት እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


አርሶአደር ሃይሉ ዴሲሳ በበኩላቸው፤ ሶስት ሄክታር የበቆሎ ማሳቸውን እየተንከባከቡ በመሆናቸው የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ አመላክተዋል።

ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር በመሆን በ30 ሄክታር መሬት ጤፍን በኩታ ገጠም በማልማት እንክብካቤ እያደረጉ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ አርሶ አደር ዳዊት አሰፋ ናቸው።

ምርታማነታቸውን ለማረጋገጥም የተሻሻለ የጤፍ ዝርያን መጠቀማቸውንና የባለሙያ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026