የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

Sep 18, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።

የክልሉ ግብርና ቢሮ የ2019 ምርት ዘመን የመስኖ እርሻ ልማት ንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።


የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ የመስኖ ልማት ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ከተረጂነት ለመላቀቅ እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ነው።

በክልሉ የመስኖ ልማት ሥራ እየተሻሻለ መምጣቱን አመልክተው፤ አርሶ አደሩም ጥቅሙን በመረዳት ከመደበኛ የግብርና ሥራ ጎን ለጎን የመስኖ ልማት ሥራን በስፋት እየተገበረ ይገኛል ብለዋል።

ከአርሶ አደሩ ባለፈ በእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች በመስኖ እርሻ ላይ ተሰማርተው የግብርና ዘርፉን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል።


ክልሉ ለመስኖ ልማት ምቹ የሆነ የውሃ ሀብት ያለው በመሆኑ አነስተኛ የመስኖ ግድቦችን በመገንባት የዘርፉን ልማት የማሳደግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የጠቀሱት።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ በበኩላቸው፤ አርሶ አደሩ በመስኖ ልማት ስራ የሚያደርገው ተሳትፎ እየጨመረ መምጣቱ ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ አስችሎታል ነው ያሉት።

በተለይ በመስኖ የሚለሙ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን ለኅብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ገበያን የማረጋጋት ሥራ ለማከናወን መቻሉንም አንስተዋል።

ባለፈው በጀት ዓመትም 57 ሺህ ሄክታር ማሳ በመስኖ በማልማት 14 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደተገኘ አመልክተው፤ በተያዘው በጀት ዓመትም 70 ሺህ ሄክታር ማሳን በመስኖ ለማልማት ወደ ሥራ መገባቱን አስታውቀዋል።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...

Sep 18, 2026

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026