የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

Sep 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና አያያዝ ላይ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ ገለጹ።

በኢሉባቦር ዞን የ2019 ዓ.ም የቡና ምርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያስችል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በመቱ ከተማ ተካሄዷል።


በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢሉባቦር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ እንዳስታወቁት፤ ባለፉት ዓመታት በዞኑ የቡና ምርት ጥራትን ለማረጋገጥ በየደረጃው ሰፋፊ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል።

በእነዚህ የተቀናጁ ስራዎችም አመርቂና ጥሩ ውጤቶች እየተመዘገቡ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በዘርፉ የተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶችን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ማሳደግ የሚያስችሉ ጥረቶች አሁንም በላቀ ትጋት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አክለው እንደገለጹት፤ የምርት ጥራትን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ሕገወጥ የቡና ዝውውርን መከላከል እና ምርቱን በወቅቱ ለገበያ ማቅረብ የዞኑ የኢኮኖሚ አቅጣጫ ነው።

በመሆኑም ከቡና አምራቾች እስከ ላኪዎች እና አመራር አካላት ድረስ ያሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለእነዚህ ነጥቦች ትኩረት በመስጠት የተቀናጀ ቁጥጥርና ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተጨማሪም የቀይ ቡና መፈልፈያ ፋብሪካዎች ቀድመው አስፈላጊውን ዝግጅት በማጠናቀቅ ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ፋብሪካዎቹ በቴክኒክና በአሰራር ረገድ ቀድመው በመዘጋጀት ከዞኑ ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርበውን የቡና ምርት ጥራትና መጠን ለማሳደግ የሚጠበቅባቸውን ሚና በብቃትና በኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባም አቶ እንዳልካቸው ጠቁመዋል።


የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ ታከለ በበኩላቸው በ2019 የምርት ዘመን ከዞኑ 62 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እቅድ መኖሩን ገልጸው፤ ለዚህ እቅድ ስኬታማነት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ተናግረዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ በ2019 ዓ.ም የምርት ዘመን የቡና ጥራትን አስተማማኝ በሆነ ደረጃ ለማስጠበቅ የገበያ ሰንሰለቱን ማስተካከልና የምርት አያያዝን ማዘመን ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በቡና ንግድ የተሰማሩት አቶ በፈቃዱ ገምቴሳ የቡና ምርት ጥራትን የማረጋገጥ ጉዳይ የአንድ አካል ብቻ ሳይሆን የሁሉንም አካላት ከፍተኛ ተሳትፎና ትኩረት የሚጠይቅ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የክትትል ሰንሰለቱ ጥብቅ መሆን እንዳለበት የጠቆሙት ተሳታፊው፤ ለቡና ምርት አያያዝም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል።

የቡና ጥራትን የማስጠበቅ ስራ በሁሉም ደረጃዎች ተመሳሳይ ትኩረት ካላገኘ በተወሰኑ ሂደቶች ብቻ ሊረጋገጥ እንደማይችል ያነሱት ደግሞ አቶ ስባቱ በቀለ ናቸው።

አያይዘውም የቡና ጥራት ከምርቱ የሚጠበቀውን ተጠቃሚነት የሚወስን ዋና ምክንያት በመሆኑ፣ ባለድርሻ አካላት በየደረጃው በሚከናወኑ የጥራት ማስጠበቅ ተግባራት ላይ በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...

Sep 23, 2026

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...

Sep 18, 2026

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026