🔇Unmute
ዲላ፣ ጥቅምት 25/2019 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ ገለጸ።
ቢሮው የ2019 በጀት ዓመት የቀጣይ100 ቀናት ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በዲላ ከተማ መክሯል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ንጋቱ ዳንሳ በወቅቱ እንዳሉት፣ በክልሉ የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተሰራ ነው።
በበጀት ዓመቱ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከ1ሺህ 700 ኪሎ ሜትር በላይ የጠጠር መንገድ ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑን አንስተው፣ ከዚህ ውስጥ 1ሺህ 100 ኪሎ ሜትሩ በመንግስት በጀት የሚከናወን መሆኑን ገልጸዋል።
ቀሪው 600 ኪሎ ሜትር መንገድ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚገነባ መሆኑንም አመልክተዋል።
በክልሉ ዛሬም በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት በአማካይ ከአንድ ሰዓት በላይ በእግር እንደሚጓዙ ያስታወሱት አቶ ንጋቱ፣ የመንገድ ልማትን በማስፋፋት ህብረተሰቡ በትራንስፖርት ሲደርስበት የነበረን እንግልት ለማስቀረት የተጀመረው ሥራ ይጠናከራል ብለዋል።

በተለይ ከብልሹ አሰራርና ከሌብነት በመራቅ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ይሰራል ብለዋል።
ህብረተሰቡም ለመንገድ ግንባታ በአይነት፣ በገንዘብና መሰረተ ልማቶችን ከጉዳት በመጠበቅ እያደረገ ያለውን እገዛ እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።
ወደከተማ የተካለሉ የገጠር አካባቢዎችን በመንገድ መሰረተ ልማት በማስተሳሰር ረገድ ከቢሮው ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን ያነሱት ደግሞ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ብዙአየሁ ታደሰ ናቸው።

በከተማው እየተገነባ የሚገኝውን የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መናኸሪያ በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃትም የጋራ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።
በመድረኩ በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ዲላ፣ ጥቅምት 25/2019 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እ...
Nov 5, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...
Oct 14, 2026
መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...
Sep 23, 2026
አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...
Sep 18, 2026