🔇Unmute
ጎንደር ፣ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ቀድመው የደረሱ ሰብሎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ የመሰብሰብ ሥራ በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ገለፁ።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የገጠር ክላስተር አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የደረሱ ሰብሎችን ከብክነት በፀዳ መንገድ የመሰብሰብ ስራ በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።
የደረሰ ሰብል ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ጉዳት እንዳይደርስበትና የድህረ ምርት ብክነትን ለመቀነስ ከላይ እስከ ታች ባለው አመራርና ሙያተኛ በቅንጅት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
በተለይም የአዝመራ ስብሰባ ወቅቱን ጠብቆ እንዲከናወንና አርሶ አደሩ በምርት ብክነት እንዳይጎዳ፣ የደረሱ ሰብሎችን በቴክኖሎጂ በታገዘ አግባብ ፈጣንና ውጤታማ በሆነ መንገድ የመሰብሰብ ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተዋል።
በግብርና ኤክስቴንሽን አርሶ አደሩን አስቀድሞ የማዘጋጀት ሥራ መጠናቀቁን ተከትሎ፣ በአሁኑ ወቅት የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት እና በጥራት ለመሰብሰብ ከ80 በላይ ኮምባይነሮች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል።
በምሥራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎንደር እንዲሁም ሰሜን ሸዋ አካባቢዎች የስንዴ ምርትን በኮምባይነር የመሰብሰብ ሥራ በስፋት እየተከናወነ እንደሆነም ለአብነት አንስተዋል።
በቀጣይም ተጨማሪ ኮምባይነሮችን ለማስገባትና ክልሉ የያዘውን የአምስት ዓመት ግብ ለማሳካት እየተሠራ ነው ብለዋል።
ለእርሻ ትራክተርና ለኮምባይን ሃርቨስተር ማሽኖች ልዩ ትኩረት በመስጠት የሜካናይዜሽን አገልግሎቱ እየሰፋ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ይህም የድህረ ምርት ብክነትን መቀነስ አስችሏል ብለዋል።
የደረሱ ሰብሎችን ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ሊከሰት ከሚችል ጉዳት ለመጠበቅም አርሶ አደሩ በተሻለ ቅንጅትና ቅልጥፍና መሰብሰብ እንዳለበት አሳስበዋል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ንጉሴ ማለደ በበኩላቸው፤ በዞኑ በመኽር ወቅቱ በሰብል ከለማው 586 ሺህ ሄክታር 187 ሺህ ሄክታሩን መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።
ከዚህ አጠቃላይ የለማ መሬትም ከ24 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
አሁን ላይ የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ በመሰብሰብ የድህረ ምርት ብክነትን መቀነስ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ይገኛል ሲሉም ገልፀዋል።
አብዛኛው የማሳ ሰብል በመድረስ ላይ ያለ በመሆኑ ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በንቅናቄ ሰብል የመሰብሰብ ሥራዎች በስፋት የሚከናወን መሆኑንም አስረድተዋል።
በዚህም የሚሰበሰቡ ምርቶች ለወጭ ንግድ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ ከማሳ እስከ መጋዘን ደረጃውን እና ጥራቱን ጠብቆ እንዲዘጋጅ በባለሙያ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በጎንደር ከተማ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እቅድ ትግበራ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል።
ጎንደር ፣ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ቀድመው የደረሱ ሰብሎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ የመሰብሰብ ሥራ በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ በም...
Nov 9, 2026
ዲላ፣ ጥቅምት 25/2019 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እ...
Nov 5, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...
Oct 14, 2026
መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...
Sep 23, 2026