የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በኦሮሚያ ክልል ስራ አጥነትን ለመቀነስና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

Aug 25, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ ፤ነሐሴ 18/2018(ኢዜአ )፡-በኦሮሚያ ክልል ስራ አጥነትን ለመቀነስና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ በክህሎት ልማት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን የክልሉ የስራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።

በኦሮሚያ ክልል ያለውን ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥርና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የስራ ፈላጊዎች መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ዘላቂ የስራ ዕድል መፍጠር የክልሉ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ቆይቷል።


ቀደም ሲል የሚደረጉ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችና የስራ ዕድል ፈጠራ ጥረቶች በቂ የቴክኒክና የክህሎት ክፍተት ባለባቸው ስራ ፈላጊዎች ምክንያት የተፈለገውን ያህል ውጤት ሲያመጡ አልታዩም።

በዚህም ምክንያት የክልሉ የስራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ችግሩን ለመፍታት የሙያና ክህሎት ስልጠናዎችን እንደ ዋነኛ መሳሪያ በመጠቀም፣ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር የተቀናጀ አሰራር በመዘርጋት ላይ ይገኛል።

ዛሬ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የምክክር መድረክም፣ ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ዜጎችን በሙያና ክህሎት ለማብቃት የሚያደርገው የዚሁ ጥረት አካል ነው።


የቢሮው ሃላፊ ኢንጂነር ኤባ ገርባ በወቅቱ፤ ስራ አጥነትን ከመሰረቱ ለመቀነስ፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና ተኪ ምርት ለማምረት በሙያ የበቃ የሰው ሃይል በጥራትና በብዛት ማፍራት ወሳኝ ነው ብለዋል።

የክልሉ ዜጎች በሙያ ራሳቸውን ችለው ከመደበኛ ስራ በተጨማሪ በክህሎትና ኢንተርፕሩነርሽፕ ራሳቸውን ማጎልበት አለባቸው ብለዋል።

ገበያው የሚፈልገውን የሰው ሃይልና የሙያ ልማት ላይ መስራት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከግብርና፣ ትምህርት ፣ ማዕድን፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ጨምሮ ከተለያዩ ሴክተሮች ጋር በጋራ እየሰራን ነው ብለዋል።

የቢሮው የክህሎት ልማት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነርሰዲን ቃድ በበኩላቸው የክህሎት ልማቱ መነሻ ገበያ ተኮር ሙያተኞችን ማፍራት ነው ብለዋል።


በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችንና አቅሞችን በመለየት የልማት ፕሮጄክቶች፣ ሆቴሎችና የቱሪዝም መስቦች እንዲሁም የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ትኩረት አድርገን አጫጭር የሙያ ስልጠና እንሰጣለን ነው ያሉት።

በአዲሱ በጀት ዓመት ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችሉ ገበያ ተኮር አጫጭር የሙያና ክህሎት ልማት ስልጠናዎች 3 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች በመስጠት ወደ ስራ ለማስገባት መታቀዱን ለአብነት አንስተዋል።

ለዚህም በክልሉ 21 ዞኖችና 23 ከተሞች ያሉትን ፀጋዎችና የገበያ ፍላጎቶችን በመለየት የክህሎት ልማት ስልጠና ይሰጣል ብለዋል።


በኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ፕሮግራሞች ዳይሬክተር እጩ ዶክተር መንግስቱ ለታ እንደገለፁት በሙያና ክህሎት የዳበረ የሰው ሃይል ለማፍራት ከስራና ክህሎት ቢሮ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመን አብረን እየሰራን ነው ብለዋል።

"በአሁኑ ወቅት ለ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የክህሎት ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል" ያሉት ዳይሬክተሩ ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችም የሙያ ትምህርት ለመስጠት 23 የሙያ አይነቶች ተለይተው መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ

በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመ...

Aug 22, 2026

የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ዘላቂ ተጠቃሚነታችንን ለማረጋገጥ አስችሎናል-አርሶ አደሮች

ደብረብርሃን፤ ነሀሴ 14/2018 (ኢዜአ)፡-በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በመሳተፍ ዘላቂ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መቻላቸውን አርሶ አደሮች ገለጹ። የሌማት ት...

Aug 21, 2026

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከማዕድን ተገቢው ገቢ እንዲገኝ በትምህርት፣ በምርምር እና በአቅም ግንባታ ዘርፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከማዕድን ተገቢውን ገቢ እንድታገኝ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት፣ በምርምር እና በአቅም ግንባታ ዘርፍ የ...

Aug 18, 2026

በክልሉ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ሥራ ገብተዋል

ሚዛን አማን፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በ2018 በጀት ዓመት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ...

Aug 14, 2026