🔇Unmute
በሙሴ መለሰ
የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል።
ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል።
ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል።
በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል።
በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል።
የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል።
ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል።
በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል።
በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል።
የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል።
በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው።

በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል።
የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመ...
Aug 22, 2026
ደብረብርሃን፤ ነሀሴ 14/2018 (ኢዜአ)፡-በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በመሳተፍ ዘላቂ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መቻላቸውን አርሶ አደሮች ገለጹ። የሌማት ት...
Aug 21, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከማዕድን ተገቢውን ገቢ እንድታገኝ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት፣ በምርምር እና በአቅም ግንባታ ዘርፍ የ...
Aug 18, 2026
ሚዛን አማን፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በ2018 በጀት ዓመት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ...
Aug 14, 2026