የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ባህር ዳር ከ337 በላይ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ታደሱ

Aug 28, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ337 በላይ የአቅመ ደካማች ቤቶችን ማደስና በአዲስ መገንባት መቻሉን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

የአስተዳደሩ ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ሰብለ ዘውዱ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በህብረተሰቡ ውስጥ ባህል እየሆነ የመጣው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት እያስቻለ ነው።

በተያዘው የክረምት ወራትም በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማሳተፍ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።

በክረምቱ እስካሁን ድረስ ከ337 በላይ የአቅመ ደካማ ወገኖች መኖሪያ ቤቶችን ማደስና በአዲስ መገንባት መቻሉን ገልጸዋል።

ጥገና ለማካሄድ በዕቅድ የተያዙ 224 መኖሪያ ቤቶችን የመጠገን ሥራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ገልጸው፣ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶችን የመገንባት ተግባርም ከ96 በመቶ በላይ መከናወኑን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የደም ልገሳና ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍን ጨምሮ በ17 ዋና ዋና ተግባራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ወይዘሮ ሰብለ አስረድተዋል።

እስካሁንም ከ234 ሺህ 600 በላይ በላይ በጎ ፈቃደኞች በገንዘን፣ በጉልበትና በእውቀታቸው አስተዋጾ ማድረጋቸውን ጠቁመው፣ በጠቅላላው ከ630 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ስራ ማከናወን ተችሏል ብለዋል።

በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አቅመ ደካማ ሰዎች፣ አረጋውያን እና የአካል ጉዳት ያለባቸው ወገኖች ተጠቃሚ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

የበርካታ ዜጎችን ችግር እየፈታ ያለውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር ህብረተሰቡ ይበልጥ ባህል አድርጎት እንዲቀጥል ትኩረት መሰጠቱንም አስገንዝበዋል።

በባህር ዳር ከተማ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰማራው ወጣት ታደለ ስማቸው በበኩሉ እንደገለጸው፣ በክረምቱ ደም በመለገስና የአቅመ ደካሞችን ቤት በመጠገን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

በበጎ አድራጎት ተግባር መሰማራቱ ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት የበኩሉን እንዲወጣ ከማድረግ ባለፈ የህሊና እርካታ እንደፈጠረለትም ተናግሯል።

በእርጅና ምክንያት ቤታቸው ፈርሶ በክረምት ለዝናብና ለውርጭ፤ በበጋ ወራትም ለፀሐይና ነፋስ ሲዳረጉ መኖራቸውን ያስታወሱት ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ እማሆይ እናንየ ታመነ ናቸው።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢያቸው የሚገኙ በጎ ፈቃደኞች ቤታቸውን አፍርሰው በአዲስ መልክ በመስራትና የቤት ዕቃ አሟልተው በማስረካባቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሐረሪ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ውጤታማ እያደረገን ነው -ባለሀብቶችና ወጣቶች

ሀረር፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ውጤታማ እያደረጋቸው መሆኑን ባለሀብቶችና ወጣቶች ገለጹ። ...

Aug 27, 2026

የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ

በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመ...

Aug 22, 2026

የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ዘላቂ ተጠቃሚነታችንን ለማረጋገጥ አስችሎናል-አርሶ አደሮች

ደብረብርሃን፤ ነሀሴ 14/2018 (ኢዜአ)፡-በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በመሳተፍ ዘላቂ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መቻላቸውን አርሶ አደሮች ገለጹ። የሌማት ት...

Aug 21, 2026

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከማዕድን ተገቢው ገቢ እንዲገኝ በትምህርት፣ በምርምር እና በአቅም ግንባታ ዘርፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከማዕድን ተገቢውን ገቢ እንድታገኝ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት፣ በምርምር እና በአቅም ግንባታ ዘርፍ የ...

Aug 18, 2026