የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

Oct 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የክልሉ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ገለፁ።

የክልሉ ግብርና፣ እንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ቢሮ "ዘመናዊ ግብርና ለሁለንተናዊ ልዕልና" በሚል መሪ ሃሳብ በጎንደር ከተማ የውይይት መድረክ እያካሔደ ይገኛል።


​የዘርፍ አስተባባሪው ድረስ ሳህሉ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂና በአዳዲስ አሰራር የዳበረ በማድረግ ምርታማነትን የማሳደግ ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

ዘርፉን በቴክኖሎጂና በአዳዲስ አሰራር የዳበረ በማድረግ ሳይንሳዊ የአመራረት ዘይቤን በመከተል የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እንደተመዘገበባቸው አንስተዋል።

"የመደመር መንግስት ትኩረት ከሰጣቸው አገር በቀል የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ ግብርና ዋነኛው ነው" ያሉት ዶክተር ድረስ ዘርፉን በማዘመን ለኢንዱስትሪ ግብአትና ለውጭ ንግድ ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል።

​እንደ ሰሊጥ፣ አኩሪ አተርና ጥጥ ያሉ ገበያ ተኮር ምርቶች ላይ በማተኮርም እድገትን ለማፋጠን የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ማረጋገጥ እንደሚገባቸው ነው ያሳሰቡት።


የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መስፍን አበጀ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በ2018/19 የምርት ዘመን አዳዲስ የግብርና አሰራሮችና ቴክኖሎጂ በመተግበር 205 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ወደ ስራ ተገብቷል ነው ያሉት።

የሚጠበቀውን ምርት ለማግኘትም አርሶ አደሩ በቂ የግብርና ኤክስቴንሽን ድጋፍ እንዲያገኝ እየተደረገ መሆኑንም አብራርተዋል።

በተጨማሪም ከሰባት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ዘመናዊ ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በመደረጉ በምርት እድገት ላይ አዎንታዊ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል።

ዘመናዊ እርሻን ለማስፋፋት በተደረገው ጥረትም የእርሻ ትራክተሮችን ቁጥር ወደ ስድስት ሺህ ማሳደግ በመቻሉ በዘመናዊ መንገድ የሚታረስ መሬት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመር መምጣቱን አስረድተዋል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚሁ መድረክ ላይ የክልል ቢሮዎች፣ የዞን መምሪያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026

በባህር ዳር ከተማ አስተማማኝ ሰላምና ተጨባጭ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...

Sep 15, 2026