🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 15/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አርአያ የሚሆኑ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኗን የዘርፉ አህጉራዊ ተቋማት መሪዎች ገለጹ።
የመደመር መንግሥት ባለፉት ዓመታት ትኩረት ከሰጠባቸው የማህበራዊ ልማት ዘርፎች መካከል የጤናው ዘርፍ ተጠቃሽ ነው።
በዚህም መሰረት ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የፖሊሲ ማሻሻያ፣ የጤና መሰረተ ልማት ግንባታና የባለሙያዎችን አቅም የሚያሳድጉ ውጤታማ ተግባራትን ተከናውኗል።
የመደመር መንግስት ከጤና ተቋማት ግንባታ ባሻገር ህብረተሰቡ አስቀድሞ ጤናውን መጠበቅ የሚያስችለውን የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።
በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ እንዲሁም የዲጂታል ጤና ሥራዎች ከእነዚህ ስኬቶች መካከል ናቸው።

የአፍሪካ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ጥምረት ፕሬዝዳንትና የምሥራቅ አፍሪካ ጥምረት ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ካውሺክ ራማያ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ውጤታማ ተግባር አከናውናለች።
የጤና ባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት፣ የጤና አገልግሎትን በማጠናከርና በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያከናወነችው ውጤታማ ተግባር ሌሎች ሊተገብሩት የሚችሉት ተምሳሌት ተግባር ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለበሽታ አጋላጭ የሆኑ ምክንያቶችን በመቀነስ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከልና መቆጣጠር የሚያስችሉ ውጤታማ ስራዎችን መስራቱንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በጤና ኤክስቴንሽን መርሃግብር፣ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት በማጠናከር ብሎም የአካባቢ ብክለትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ሕጎችና ደንቦችን በመተግበር ረገድ አርአያ የሆነ ተግባር አከናውናለች ብለዋል።
የአፍሪካ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ጥምረት ዋና ዳይሬክተር ፈርዲናንድ ሶኒዩ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ውጤታማና አስደናቂ ተግባራትን ማከናወኗን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ለአሁኑና ለመጪው ትውልድ ጤናማነት መሰረት የሚሆን ውጤታማ ስራ እያከናወነች መሆኑንም አስረድተዋል።
አፍሪካ በርካታ ወጣቶች ያሏት አህጉር በመሆኗ ከኢትዮጵያ ተግባራዊ እርምጃዎች ወሳኝና ለሌሎች ምሳሌ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ጥምረት ሥራ አስኪያጅ ማህሌት ወርቁ ከዚህ ቀደም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በቂ ትኩረት ሳያገኙ መቆየታቸውና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዘርፉ ለውጥ እየታየ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም የኮሪደር ልማትና የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች ቅድመ መከላከል ላይ ያተኮረ የአኗኗር ዘይቤ እንዲኖር ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው አስረድተዋል።
አዲስ አበባ፤ ህዳር 12/2019(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ በሕግ፣ በኢኮኖሚ የዕድገት ፍላጎትና በመልክዓ ምድራዊ ቅርበት ላይ የተመሰረተ...
Nov 23, 2026
ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...
Oct 20, 2026
ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...
Oct 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...
Sep 30, 2026