የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ባለፉት ዓመታት የተከናወነው ውጤታማ ሪፎርም የኢኮኖሚ ዕድገቱን የማይበገር አድርጎታል 

Nov 27, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17/2019 (ኢዜአ)፦ባለፉት ዓመታት የተከናወነው ውጤታማ ሪፎርም የኢኮኖሚ ዕድገቱን የማይበገር አድርጎታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ፣ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማብራሪያቸው፤ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በኢንዱስትሪ፣ በከተማ ልማት፣ በሜጋ ፕሮጀክቶች እንዲሁም በፋይናንስ ዘርፎች የኢኮኖሚ ማገገም እየታየ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ የጀመረችውን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ለውጥ በማጠናከር ከአፍሪካ ሀገራት ያላትን ደረጃ ይበልጥ ለማሻሻል በቀጣይነት ይሰራል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ሰፊ የልማት አቅም ያላቸውን ቆላማ አካባቢዎች በመሠረተ ልማትና በሰው ኃይል ዝግጁነት ማልማት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ቆላማው ክፍል ያለውን ሰፊ መሬትና የውኃ ሀብት ወደ ልማት ለመቀየር የመንገድ፣ የባቡርና የኃይል መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የሰው ኃይሉን ክህሎትና ዝግጁነት ከዘመናዊ እርሻና ኢንዱስትሪ ጋር ማጣጣም ቁልፍ ተግባር መሆኑን አመልክተዋል።

በሶማሌ ክልል ጎዴና ሽኒሌ የተሠሩ የመስኖ ልማቶች፣ በአፋር ተንዳሆ፣ ከሰምና ሎጊያ እንዲሁም በኦሮሚያ ጨልጨልና ወልመል የተከናወኑ ሥራዎችና በቦረና የተገነቡ ከአሥር በላይ አነስተኛ ግድቦች ለዚህ ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ቀደም ብሎ በተደረገ ሰፊ ዝግጅትም የኤልኒኖ የአየር ንብረት ጫና ከፍተኛ ጉዳት ሳያስከትል ማለፉንና የውኃ ማቆያና የጥንቃቄ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ቀጣናዊ የጋራ ተጠቃሚነትንና ዕድገትን የሚያረጋግጥ መሰረታዊ ጉዳይ ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 12/2019(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ በሕግ፣ በኢኮኖሚ የዕድገት ፍላጎትና በመልክዓ ምድራዊ ቅርበት ላይ የተመሰረተ...

Nov 23, 2026

በሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተጀምሯል

ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...

Oct 20, 2026

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026