የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ትናንት ማምሻውን በኢትዮጵያ የታዩት ቁሳዊ አካላት የቻይና ሺ ጂያን-19 ሳተላይት ቀሪ አካል ሊሆኑ ይችላሉ - የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ

Jan 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 2/2017(ኢዜአ)፦ በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የኢትዮጵያ ክፍሎች ትናትን አመሻሽ የታዩት ቁሳዊ አካላት የቻይና ሺ ጂያን-19 (ShiJian-19) የተባለ ሳተላይት ቀሪ አካል ሊሆኑ እንደሚችል ያመለክታል ሲል የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ አስታወቀ።

ሶሳይቲው በትናንቱ እንግዳ የሕዋ ክስተት ዙሪያ ከተለያዩ የሕዋ አካላት መከታተያ እና የመረጃ ቋቶች ያገኘናቸውን መረጃዎች በማጠናቀር ባደረግነው ጥልቅ ትንተና መሰረት ሳይንሳዊ መላምት ላይ መድረሱን ገልጿል።

በመረጃው መሰረት የሕዋ አካሉ ባለቤትነቱ የቻይና የሆነ ሺ ጂያን-19 (ShiJian-19) የተባለ ሳተላይት ቀሪ አካል ሊሆን እንደሚችል ያመላክታል ብሏል።

ሳተላይቱ መስከረም 17 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ምህዋር መወንጨፉንና ተልዕኮውን ጨርሶ ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ መሬት መመለሱን አመልክቷል።

ነገር ግን ሳተላይቱ በተልዕኮው ላይ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ክፍሎቹ ከዋናው ሳተላይት ተነጥለው በምህዋር ላይ ሲዞሩ መቆየታቸውን ነው ያስታወቀው።

ሶሳይቲው ለትንተናው የተጠቀመባቸው መረጃዎች ከሶስተኛ ወገን የመረጃ ቋቶች የተገኙ በመሆኑ የተረጋገጠ መረጃውን የሳተላይቱ ባለቤት ሃገር ቻይና እስክታረጋግጥ መጠበቅ እንደሚገባ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.