የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>የባለፉት ዓመታት ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት አሳድገዋል</p>

Feb 24, 2025

IDOPRESS

ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።

በሐረር ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሀገር አቀፍ ሕዝባዊ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እንዳሉት ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸው የልማት፣ የሰላም፣ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ስራዎች ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው።



በተለይም ህዝብና መንግስትን በማስተባበር ሀገርን ማልማትና ማሻገር እንደሚቻል በግልጽ የታየበት መሆኑንም አመልክተዋል።

በሐረሪ ክልልም የተከናወኑ የልማት ስራዎች ነዋሪውን ተጠቃሚ ያደረጉና የህዝቡን የልማት ጥያቄ የመለሱ ናቸው ብለዋል።

መድረኩም ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውንና በቀጣይ በሚያከናውናቸው ስራዎች ላይ የህዝብ ድጋፍና ትብብር ለማጎልበት የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም ያልተፈቱና ምላሽ ያላገኙ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና ሌሎች ስራዎችን ለመፍታት ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።

በመድረኩ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ በብልፅግና ፓርቲ የአፋር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር፣ በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ እና የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.