የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው ጉዳይ አይደለም- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ</p>

Feb 28, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በግብርናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ እና ግብዓት አጠቃቀምን በማሻሻል እንዲሁም አዳዲስ አሰራሮችን በማላመድ የዘርፉን ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የምግብና ስርዓተ ምግብ ዋስትናና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው፤ የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚያሻ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በተለይ በመኸር እርሻ የተመዘገበውን አመርቂ ውጤት በበልግ አዝመራ ሥራ በመድገም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የተጀመረውን ሽግግር ማፅናት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለዚህ ደግሞ አመራሩ በቁርጠኝነት እንዲሰራ ማሳሰባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

ለታለመው የበልግ አዝመራ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ እና ሌሎችም ኢንሼቲቮች አመራሩና ባለሙያው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲሰሩ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.