አዲስ አበባ፤ጥር 5/2017(ኢዜአ)፡-ባለፉት ስድስት ወራት መንግስት ለነዳጅ 137 ቢሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።
ባለፉት ጊዜያት ነዳጅ በመደበቅ ሰው ሰራሽ ችግር እንዲፈጠር ባደረጉ 250 የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንም ጠቁመው ቦቴዎቹም ለስድስት ወራት ከነዳጅ ማመላለስ እንዲታገዱ መደረጉንም ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ የነዳጅ ግብይትን እና የዋጋ ማሻሻያውን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም መንግስት የኑሮ ውድነትን ለመከላከል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ተግባራዊ በማድረግ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በዚህም መንግስት በተለያዩ ምርቶች ላይ ድጎማዎችን በማድረግ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳይጎዱ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወኑንና አሁንም አጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል።
ባለፋት ስድስት ወራትም መንግስት ለነዳጅ ድጎማ 137 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን ገልጸዋል።
ከዚህ ውጪም በታለመለት የነዳጅ ድጎማም የህዝብ ማመላለሻ እና ለከተማ አውቶቡሶች ከ463 ሚሊዮን ብር በላይ ድጎማ መደረጉንም ጠቁመዋል።
የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጠቆሙት ሚኒስትሩ መንግስት ከፍተኛውን የነዳጅ ዋጋ ተሸክሞ ድጎማም በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
መንግስት በአሁኑ ጊዜ በናፍጣ ምርት ላይ በሊትር 28 እንዲሁም በቤንዚን ላይ በሊትር 21 ብር ድጎማ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የነዳጅ ኮንትሮባንድን ለመከላከል፣ አቅርቦትን ለማሳለጥ እና ስርጭት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ባለፉት ጊዜያት ነዳጅ በመደበቅ ሰው ሰራሽ ችግር እንዲፈጠር ባደረጉ 250 የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንም ጠቁመው ቦቴዎቹም ለስድስት ወራት ከነዳጅ ማመላለስ እንዲታገዱ መደረጉንም ጠቁመዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ 19 የነዳጅ ማደያዎች ለስድስት ወራት ከነዳጅ ግብይት መታገዳቸውንም ገልጸው ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ቅጣት መተላለፉንም ጠቁመዋል።
በሌላ መልኩ 385 ሺህ ሊትር ነዳጅ መወረሱን የገለጹት ሚኒስትሩ ተጨማ 35 ማደያዎች ላይም እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።
መንግስት ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት በሚያደርጉ አካላት ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር በማጠናከር በአጥፊዎችም ላይ አስፈላጊው እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግስት ህገ- ወጥነትን ለመከላከል የሚያደርገውን የተቀናጀ ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው የነዳጅ ማደያዎች ግብይት በዲጂታል የክፍያ አማራጭ ብቻ እንዲሆንም አሳስበዋል።
ሚኒስቴሩ ከነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ጋር በመሆን በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተሞች በሚገኙ 95 ማደያዎች ላይ ባደረገው ምልከታ 22 የሚሆኑ ማደያዎች ችግር ያለባቸው መሆኑን መለየቱን ገልጸዋል፡፡
በዚህም ማሽን ተበላሽቷል በማለት ነዳጅ እያለ አለመሸጥ፣ የነዳጅ ግብይት ሂደቱን በማዘግየት የዋጋ ጭማሪ ሲመጣ ተጠቃሚ ለመሆን ተገልጋይን ማንጋላታትን ጨምሮ ሌሎችንም በምልከታው ማረጋገጡን ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025