አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2017(ኢዜአ)፡- በዘንድሮው የበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት እስካሁን 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ በበጋ ወራት የመኸር ሰብልን በአግባቡ በመሰብሰብ ብክነትን ለማሳቀረት እንዲሁም የበጋ መስኖ ልማትን ማጠናከር ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በ2016/2017 የመኸር ምርት ዘመን በዘር ከተሸፈነው 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ እስከ ጥር ወር መጀመሪያ ቀናት ድረስ ብቻ በ18 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር ላይ የደረሰ ሰብል መሰብሰቡን ተናግረዋል።
ከዚህም 420 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገኝቷል ነው ያሉት።
በዋና ዋና ሰብሎች በቆሎ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ሩዝ እና አኩሪ አተር ከተሸፈነው 12 ነጥብ 17 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 10 ነጥብ 6 ሚሊዮኑ መሰብሰቡን ገልጸው፤ ከዚህም 289 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን አንስተዋል።
ወቅቱን የጠበቀ የግብርና ግብዓትን ተደራሽ ማድረግ፣ የክላስተር እርሻና የተቀናጀ የግብርና ስራ ለውጤታማነቱ ወሳኝ ሚና መጫወቱን ጠቅሰዋል።
እንደ ሀገር ለበጋ መስኖ ልማት በተሰጠው ትኩረት በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ በበጋ ስንዴ ልማት 4 ነጥብ 27 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 172 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ለማግኘት ታቅዷል ብለዋል።
ከ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት እስካሁን የታረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታሩ በዘር መሸፈኑንና ሰብሉም በጥሩ ይዞታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የበጋ መስኖ ልማት ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የያዘችውን ግብ ለማሳካት ጥሩ መሰረት እየሆነ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በበጋ ወራት የመስኖ ልማትን ለማስፋፋት ትላልቅ ግድቦች፣ የኤሌክትሪክ የመንገድ፣ የቱሪዝም መሰረተ ልማቶች በመከናወን ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት።
የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት፣ የሌማት ትሩፋት፣ የከተማ ግብርና ሥራዎች በስፋት እየተተገበሩ መሆኑንም አስረድተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025