አዲስ አበባ፤ጥር 9/2017(ኢዜአ)፦የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ምቹ የኢኮኖሚ መደላድል የፈጠረ እና ሕገ-ወጥነትን ወደ ሕጋዊ አሰራሮች የመለሰ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ኢትዮጵያን ከብድር ጫና የሚያላቅቅ መሆኑን ሚኒስትሩ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ መግባቷ ዘላቂ የልማት ፋይናንስ በመፍጠር ለበርካታ ዘርፎች መነቃቃት መፍጠሩን ተናግረዋል።
በሀገሪቱ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚን መፍጠር፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ሴክተሩን ማሻሻል እንዲሁም የዘርፎችን ምርታማነት በማሳደግ የመንግስትን የማስፈፀም አቅም መጨመር የማሻሻያው የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑ አብራርተዋል።
የውጭ ምንዛሬ ዋጋ በገበያው እንዲተመን መደረጉ፣ አምራቾች የልፋታቸውን እንዲያገኙ እንዲሁም ኮንትሮባንድና መሰል ሕገ-ወጥ ተግባራት እንዲገቱ የሚያስችል መሆኑንም አመላክተዋል።
በዚህም የወጪ ንግድ እድገትን በታለመለት መልኩ ማስኬድ መቻሉን አንስተዋል።
ማሻሻያው የባንኮች የቁጠባ መጠን እንዲጨምር ማድረጉንም ጠቁመው፥ ብሔራዊ ባንክ ከቀደመው ጊዜ በበለጠ የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዲኖረው ማስቻሉን ነው ሚኒስትሩ የገለጹት።
ማሻሻያው ምቹ የኢኮኖሚ መደላድል የፈጠረ እና ሕገ ወጥነትን ወደ ሕጋዊ አሰራሮች የመለሰ ነው ብለዋል።
የወርቅ አምራቾች በዓለም አቀፍ የዋጋ ተመን በመሸጣቸው ወርቅን በኮንትሮባንድ ከመሸጥ ይልቅ ለማዕከላዊ ገበያ ለብሔራዊ ባንክ እንዲሸጡ መነሳሳት መፍጠሩንም ተናግረዋል፡፡
በዚህም ብሔራዊ ባንክ በታሪኩ ከፍተኛ የወርቅ መጠን በመግዛት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
መንግስት ለአፈር ማዳበሪያ፣ ለነዳጅ፣ ለዘይት፣ ለመሰረታዊ ሸቀጦች፣ ለመንግስት ሰራተኞች ደሞወዝ እና ለከተማ እና ገጠር ሴፍቲኔት የሚውል በዓመት ከ400 ቢሊዮን ብር በላይ መንግስት ድጎማ ማድረጉን ተናግረዋል።
በቀጣይም ምርታማነትን ማሳድግ እና ማሻሻያውን በታለመለት መልኩ ማስኬድ የትኩረት አቅጣጫዎች ሆነው እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025