አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ገፅታ የቀየሩና ብልፅግናዋን የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን መመልከታቸውን ዳያስፖራዎች ገለጹ።
መንግስት በሀገራዊ ለውጡ በተከተለው አዲስ የልማት ፖሊሲ ግብርና፣ ቱሪዝም፣ ዲጅታል ኢኮኖሚ፣ አምራች ኢንዱስትሪና ማዕድን ዘርፎች ላይ ሚዛናዊ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
በሀገር ልማት ላይ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እንዲጎለብት ባደረገው የማሻሻያ ሥራ በርካታ ዳያስፖራዎችን ጨምሮ ባለሀብቶች ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶችና ኢንቨስትመንት ላይ እየተሳተፉ ነው።
ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት የመጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያን እድገትና ብልፅግና የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች እውን ሆነው መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በኬኒያና ካናዳ ለረጅም ዓመታት የኖሩት አቶ አብርሃም ጥላሁን በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች መሰማራታቸውን ጠቅሰዋል።
በኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ እየተካሔዱ ያሉ የልማት ስራዎች ዓለም አቀፍ ደረጃን ያሟሉ መሆናቸውን መመልከታቸውንም አንስተዋል።
በቱሪዝም ዘርፉ በገበታ ለሀገር የተገነቡትን ወንጪንና ሃላላ ኬላን የማየት ዕድል እንዳጋጠማቸው የጠቀሱት አቶ አብርሃም፥ አስደናቂ የግንባታ ጥበብ ያረፈባቸውና ምቹ የመስህብ ስፍራ ናቸው ብለዋል።
የመዳረሻ ስፍራዎቹን በመገንባት ሂደት የታየው የፕሮጀክት አፈጻጸም ውጤታማነትም በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሃብቶችን የሚያነሳሳ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግስት ለዳያስፖራው የሰጠውን ትኩረት በመጠቀም ከራስ አልፎ ለሀገር የሚተርፍ ስራ ለመስራት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኑሯቸውን በዱባይ ያደረጉትና በዚያው ሀገር በተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ የተሰማሩት አቶ መሃመድ ኑር ካሶ መንግሥት ለዳያስፖራው ያስተላለፈውን ጥሪ በመቀበል ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ማየታቸውን ጠቅሰው፥ ባዩት ነገርም በእጅጉ መደነቃቸውን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በፈጣን እድገት ላይ እንደምትገኝ በተጨባጭ የሚያሳዩ ሥራዎች በሁሉም አቅጣጫ መኖራቸውንም ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ጠቁመው፥ መንግስት የሚፈልጉትን ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሆነ አንስተዋል።
አዲስ አበባ ከወትሮ ገፅታዋ የላቀ ውበት ተላብሳና ተለውጣ በማየታቸው ደስታና ግርምትን እንደፈጠረባቸው የሚናገሩት ደግሞ በስዊዘርላንድ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ የሆኑት ወይዘሮ ኤሚ በቀለ ናቸው።
በከተማዋ ያዩት የልማት ሥራ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ተግባራት ላይ እንዲሰማሩ መነሳሳት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።
መንግስት በተለያየ ወቅት የሚያቀርበው ወደ ሀገር ቤት ጥሪ ዳያስፖራው ከሀገሩ ጋር ያለውን መስተጋብር እንዲያጠናክር የሚያስችል መሆኑንም ዳያስፖራዎቹ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025