የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>በተለያየ ምክንያት ስራ አቁመው የነበሩ ከ625 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ ተደርጓል- ሚኒስትር መላኩ አለበል</p>

Jan 22, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ጥር 13/2017 (ኢዜአ)፦በተለያየ ምክንያት ስራ አቁመው የነበሩ ከ625 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አማካኝነት ወደ ስራ መመለሳቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የእቅድ አፈፃፀም የስትሪንግ ኮሚቴ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በዚሁ ወቅት እንደገለፁት የኢትዮጵያ ታምርት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ወደ ስራ ከገባ ጀምሮ በተለያየ ምክንያት ስራ አቁመው የነበሩ ከ625 በላይ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ተመልሰዋል።

የአምራች ኢንዲስትሪዎች የማምረት አጠቃቀም 46 በመቶ የነበረ መሆኑን የጠቀሱት አቶ መላኩ፥ ንቅናቄው ከተጀመረ አንስቶ በአማካይ የማምረት አቅም ወደ 61 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።


ንቅናቄው ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በመንግስት ትኩረት እንዲያገኝና በዘርፉ ችግሮች ዙሪያ ተከታታይነት ያለው ውይይት በማድረግ ለችግሮቹ የመፍትሔ ባለቤት በመሆን በጋራ መስራት በመቻሉ የማምረት አቅም አጠቃቀም፣ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች መተካት፣ በራስ ምርት የመኩራትና የመጠቀም ባህል እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

በውይይቱ ላይ የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አፈፃፀም መቅረቡን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.