ድሬደዋ ፤ጥር 13/2017(ኢዜአ)፦በድሬዳዋ በግማሽ በጀት ዓመት ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ስራ ገብተዋል ሲል የአስተዳደሩ ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለፀ።
በኢንቨስትመንት ስራ ላይ ለመሰማራት ወደ ከተማዋ እየገቡ የሚገኙ ባለሃብቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የአስተዳደሩ ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለፀ።
በዚህም በግማሽ በጀት ዓመት ብቻ ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ስራ ገብተዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዲ ሙክታር ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ አገራዊ የለውጥ ሪፎርሙን ተከትሎ መዋዕለ ነዋያቸውን በኢንቨስትመንት ስራ ላይ ለማዋል ከአገርና ከውጭ አገራት የሚመጡ ባለሃብቶች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል።
ድሬዳዋ ለጅቡቲ ወደብ ያላት ቅርበትና በመሠረተ ልማቶች መተሳሰሯ ድሬዳዋን ተመራጭ መዳረሻ ማድረጉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ታምርት አገራዊ የኢንዱስትሪ ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እየተደረገ የሚገኘው የተቀናጀ የመሠረተ ልማትና የፋይናንስ አቅርቦት፣ሙያዊ ድጋፍና ፈጣን አገልግሎቶች ወደ ስራ የሚገቡ ባለሀብቶች እንዲጨምር ማገዙን ነው የገለፁት።
እነዚህ ድጋፎች የተዘጉ እና በግንባታ ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ማምረት እንዲገቡ ማስቻሉንም ጠቁመዋል።
በቢሮው የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ጥናትና መረጃ ቡድን አስተባባሪ አቶ አበራ መንግስቱ በበኩላቸው፤ በግማሽ በጀት ዓመቱ የተደረጉ ድጋፎችና ምቹ አሠራሮች በመጠቀም ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ስራ ገብተዋል ብለዋል።
በማኑፋክቸሪንግ፣ በአገልግሎት፣በግብርናና በኮንስትራክሽን ዘርፎች የተሰማሩት ባለሃብቶቹ ወደ አገልግሎት ሲገቡ ከ34 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩም ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የፋይናንስ፣ የመሬት አቅርቦትና የግብዓት ችግሮች ከተቃለሉላቸው ግዙፍ ፋብሪካዎች አንዱ የተለያዩ የብረታ ብረት ውጤቶችን የሚያመርተው ድሬ ስቲል ፋብሪካ ተጠቃሽ ነው።
የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ዩሱፍ እንዳሉት፤ በአገር አቀፍና በድሬዳዋ አስተዳደር ለባለሃብቶች እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተስፋ ሰጪ ስራዎችን ለመስራት አስችሏል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በተደረገው የተቀናጀ ድጋፍና ከትትል ዘጠኝ የተዘጉና በግንባታ ላይ የቆዩ ፋብሪካዎች ወደ ማምረት እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን፤ ፋብሪካዎቹ ከ1 ሺህ 170 በላይ ሰዎች ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠራቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025