አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፡- የጃፓን ልማት ኢንስቲትዩትና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በትብብር መስራት በሚችሉባቸውን ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
የኩባንያዎቹ የስራ ኃላፊዎች በተለይም ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን ውጤታማ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት መክረዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የጃፓን ልማት ኢንስቲትዩት ፕሬዝዳንት ሾይቺ ካባያሽን (ዶ/ር) በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በትብብር የመስራት ፍላጎት እንዳለ ገልጸዋል።
የጃፓን ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ፕሬዚዳንት ሾይቺ ካባያሽን (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እምቅ አቅም እንዳላት እና ለማልማት አመቺ መሆኗን እና በኢትዮጵያም ለዘርፉ ዕድገት የማማከር ስራ እንደሚያከናውን አመልክተዋል።
የጃፓን ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ከ75 በላይ በሚሆኑ የተለያዩ ሃገራት ላይ ከ350 በላይ የሚሆኑ ሃገር አቀፍ ፕሮጀክቶችን በማማከርና ወደ ትግበራ በማስገባት ከ40 ዓመት በላይ የዘለቀ ልምድ ያለው ኩባንያ መሆኑን ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025