የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የሚከናወኑ የተለያዩ ስራዎችን ይመለከታሉ</p>

Feb 6, 2025

IDOPRESS

ጂንካ፤ ጥር 28/2017(ኢዜአ):- የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሰቢ አቶ አገኘሁ ተሻገር በዩኒቨርሲቲው እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ ስራዎችን ይመለከታሉ።

አፈ ጉባኤው የዩኒቨርሲቲውን የመማር ማስተማር፣ የጥናትና ምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን እንደሚመለከቱም ተገልጿል።


በተለይ ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያከናውናቸውን ተግባራት እንደሚገመግሙም ታውቋል።

አቶ አገኘሁ ተሻገር ጂንካ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ኩሴ ጉዲሼ(ዶ/ር) እና የአሪ ዞን ከፍተኛ አመራር አባላትና የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.