የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>ዓለም አቀፍ የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ጉባዔ በኢትዮጵያ ይካሄዳል</p>

Feb 7, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፡- ዓለም አቀፍ የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ጉባዔ ከየካቲት 5 እስከ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ይደረጋል።

በጉባዔው ላይ የሀገራት መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ።

ጉባዔው ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ቴክኖሎጂዎች ትግበራ ፖሊሲን ለመቅረፅ እና የአፍሪካን የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ መሆኑን ከመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ውይይቱ እንደ ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ሆኖ እንደሚያገለግልም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.