የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማስቀረት የመንገዶች ማሻሻያ ግንባታ እየተከናወነ ነው</p>

Feb 7, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2017(ኢዜአ)፡- በአዲስ አበባ መግቢያና መውጫ እንዲሁም በሸገር ከተማ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማስቀረት የአዲስ እና የነባር መንገዶችን ደረጃ የሚያሻሽሉ ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ።

አስተዳደሩ የአዲስ አበባና የሸገር ከተማን የሚያገናኙ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዳርቻ የሚያልፉ የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ እና ነባሮቹን የማስፋት ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

አስተዳደሩ ዘጠኝ የመንገድ ፕሮጀከቶች ግንባታ መጀመሩንና ግንባታዎቹ በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም የትራፊክ ፍሰቱን ማሳለጥ የሚያስችሉ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

የሸገር ከተማን የሚያቋርጡ እና ወደ አዲስ አበባ በሁሉም አቅጣጫ የሚያስገቡ መንገዶች ጠባብ እና ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ያለባቸው መሆኑ በጥናት መለየቱ ተገልጿል።


በዚህም የአዲስ አበባ ሆለታ መንገድ ማሻሻያ ፕሮጀከክት አካል የሆነው ከኮልፌ ኖክ - አሸዋ ሜዳ -ኬላ 14 ነጥብ 73 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው እና 50 ሜትር ስፋት ያለው የመንገድ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል።

ፕሮጀክቱን የሚሰራው የዓለም ገና ዲስትሪክት ቡድን መሪ ኢንጅነር ዮሐንስ ዮናስ መንገዱ ደረጃውን የጠበቀና በአንድ ጊዜ ስምንት ተሽከርካሪዎችን ማሳለፍ የሚችል መሆኑን ተናግረዋል።

ሌላው ከእንጦጦ ማርያም - ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል 4 ነጥብ 74 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የመንገድ ግንባታ ስራ በ18 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት እየተከናወነ ይገኛል።

ከስፔስ ኦብዘርቫቶሪ - ጫካ መንደር ፕሮጀክት 9 ነጥብ 1 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን በ25 ሜትር ስፋት ግንባታው እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል።

መንገዶቹ በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቁ በመጥቀስ ግንባታዎቹ ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ ከዚህ በፊት የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ከመቅረፍ ባለፈ በፍጥነት ወደ ሚፈልጉት ቦታ ለመሄድ እንደሚያስችላቸው ተስፋ አድርጓል።


በሸገር ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አለምነህ ነጋሳ እና አቶ ቶለሳ ያዳቴ አሁን ያለው መንገድ ጠባብ በመሆኑ አጭር ኪሎ ሜትር ለመጓዝ ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚወስድባቸው ተናግረዋል።

መንገዱ ጠባብ መሆኑን ተከትሎ በስራ መግቢያና መውጫ በትራፊክ መጨናነቅ የተነሳ ወደ ሥራ ለመሄድና ወደ ቤት ለመመለስ አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመንገዱ ግንባታ ሲጠናቅ ይህንኑ ችግራቸውን እንደሚቀርፍላቸው ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።


መንገዱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸው ለግንባታው ተብለው የተለዩ ቤቶችን ሕዝቡ ቀድሞ ማንሳቱንም ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ከእንጦጦ - ኮተቤ ፕሮጀክት 18 ኪሜ ርዝመት ያለው ሲሆን በ31 ሜትር ስፋት ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የጣፎ አደባባይ - ለገዳዲ - ኩራ - ጂዳ መንገድ ግንባታ የ17 ኪሎ ሜትር ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ከአስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያሳል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.