አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፡- ከአራት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ(ዶ/ር) የ2017/18 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ግዥን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም መንግስት ለግብርናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ተከትሎ በዘርፉ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል፡፡
መንግስት ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት ከሚሰራባቸው ጉዳዮች አንዱ የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዚህም ለ2017/18 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ከጂቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ስራ በከፍተኛ ትጋት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በበጀት አመቱ 24 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ለመፈፀም ታቅዶ 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ግዥ መፈፀሙን ተናግረዋል።
ከተገዛው 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ውስጥ 6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል የሚሆነው ጂቡቲ ወደብ መድረሱን በመጥቀስ አሁን ላይ ከ4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025