አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከተለያዩ ተቋማት ጋር የመጠጥ ውሃ ግንባታ እና የማማከር ኮንትራት አስተዳደር ስራዎችን የተመለከቱ ሁለት የውል ስምምነቶች ተፈራርሟል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) እና የየተቋማቱ ተወካዮች ናቸው።
የመጀመሪያው ስምምነት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በዋን ዋሽ ፕሮግራም የሚተገበረው የባለብዙ መንደር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አካል እንደሆነ ተገልጿል።
በዚህም በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ የአጋም በር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ የእቃ አቅርቦትን ጨምሮ ከ631 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግ ታውቋል።
የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ከ21 ሺህ በላይ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ እና በ18 ወራት ተገንብቶ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ሁለተኛው ስምምነት በሃዋሳ ዙሪያ ወረዳ ለሚገነባው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የማማከርና ኮንትራት አስተዳደር ስራዎች ላይ ያተኮረ ነው።
አጠቃላይ ስራው 15 ወራት እንደሚቆይ እና ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበት ተመላክቷል።
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው ጊዜ በጥራት ተገንብተው የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ፍላጎት እንዲያሟሉ ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025