አዲስ አበባ፤ የካቲት 02/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በበጋ መስኖ ስንዴ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።
ጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 6ኛ የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ በአዳማ እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በጨፌው መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እንዳሉት በበጋ መስኖ ስንዴ 3 ነጥብ 32 ሚሊዮን ሄክታር የማሳ ዝግጅት ተደርግል።
በዚህም እስካሁን 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል ብለዋል።
የክልሉ መንግሥት ለቡና፣ ሻይ ቅጠል እና ለአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመው ለ2018 የሚተከል ከ839 ኪሎ-ግራም በላይ የሻይ ቅጠል ዘር መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
ከቡና ችግኝ ዝግጅት አኳያም 2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ችግኞችን በማዘጋጀት እንክብካቤ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት 14 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል የቡና ምርት መሰብሰቡን ነው የገለጹት።
የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅትን በተመለከተ በመደበኛ 173 ሜትር ኪዩቢክ ኮምፖስት እንዲሁም በትል አማካኝነት 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ማዘጋጀት መቻሉን አመልክተዋል።
የአፈር አሲዳማነት ለመቀነስ በተሰራው ስራም 63 ነጥብ 5 ኩንታል ኖራ ማዘጋጀት መቻሉንም ጠቁመዋል።
የተፈጥሮ ሃብቶችን በማልማት የቱሪዝም ገቢን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም ከ1 ሺህ 48 ሄክታር መሬት በላይ የሚሸፍኑ 6 የኢኮ-ቱሪዝም ቦታዎችን መለየት መቻሉንም ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025