አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፡- በመስኖ ልማትና በአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችል ጉባኤ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ጉባኤው ከየካቲት 5 እስከ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ይህንኑ አስመልክቶ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ለመከላከል በርካታ ስራዎችን እያከናወነች ትገኛለች።
ለአብነትም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የሌማት ትሩፋት፣ የውሃ አማራጭን የማስፋት ስራዎችን ጠቅሰዋል።
ጉባኤው የመስኖ ልማትን፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን መከላከል፣ ዓለም አቀፍ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን መቅሰም ዋነኛ ዓላማው መሆኑን አብራርተዋል።
ጉባኤው የመስኖ ልማትና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ለመቋቋም የሚያግዝ ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ ለማግኘት እንደሚረዳም ተናግረዋል።
በመድረኩ ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ የዘርፉ የስራ ሃላፊዎች፣ ተመራማሪዎች፣ ተጋባዠ እንግዶችና ከ1 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይገኙበታል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያከናወነቻቸው ተግባራት በተለይም በስንዴ ልማት ዙሪያ ያላትን ልምድ እንደምታጋራም ገልጸዋል።
እንዲሁም በዘርፉ ቴክኖሎጂያዊ አሰራሮችን ማጎልበት፣ አካታችነትንና አሳታፊነትን ማረጋገጥና የመንግስትና የግል አጋርነትን ማጠናከር ሌላኛው የጉባኤው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም አብራርተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025