ባህርዳር፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ለ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ ስራና ስልጠና ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ስራና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገበያው(ዶ/ር)፤ የብልፅግና ፓርቲ በ2ኛ መደበኛ ጉባኤው ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ለስራ እድል ፈጠራ የተሰጠውን ትኩረት በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በፓርቲው ጉባኤ የተቀመጠውን አቅጣጫ መሰረት በማድረግ በክለሉ ለስራ እድል ፈጠራ በቅንጅትና በልዩ ትኩረት ለመስራት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም በማኑፋክቸሪግ፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በሌሎችም መስኮች ሰፊ የስራ እድል መፍጠር የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጨምረው አንስተዋል።
የዜጎችን በተለይም የወጣቶችን ክህሎት በማጎልበትና በማሰልጠን በውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር የሚደረገው ትብብር የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።
በመጀመሪያው የፓርቲው ጉባኤ የተቀመጠውን አቅጣጫ በመከተል በክልሉ ለ3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እደል መፍጠር መቻሉን አስታውሰው ለቀጣይ ስራዎች የተሻለ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በክልሉ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ለ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ይሰራል ብለዋል።
ለእቅዱ ማሳካትም የመንግስት ጥረት እንዳለ ሆኖ የባለሃብቶችና የአጋር አካላት ትብብር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025