አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ኮንፍረንስ የማስተናገድ አቅሟ እየጨመረ መምጣቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ፡፡
38ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ እና 46ኛው የሥራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ የእንግዶች አቀባበል መርሃግብር የብሔራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በተገኙበት በማርች ባንድና በሌሎች የጎዳና ላይ ትርኢቶች በደመቀ መልኩ ተጀምሯል።
በዚሁ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ 38ኛውን የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በተሳካ መልኩ ለማስተናገድ አብይ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከፍተኛ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡
አብይ ኮሚቴው 35 ተቋማትን የያዘ ብሄራዊ ኮሚቴ በማዋቀር የተሟላ ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰዋል።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ የማስተናገድ አቅሟ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
ጉባኤውን አስመልክቶ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማትና ለሚመለከታቸው አካላት በቂ ስልጠና መሰጠቱንም ተናግረዋል፡፡
በዚህም እንግዶቹን በተሟላ መልኩ የሚያስተናግዱ በጎ ፍቃደኞችን ጨምሮ ለሆቴሎች፣ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ለአሽከርካሪዎች በቂ ስልጠና በመስጠት ለጉባኤው ዝግጁ ማድረግ መቻሉን ነው ያስረዱት፡፡
አዲስ አበባ እንግዶቿን ለመቀበል ውብና ጽዱ ሆና እየተጠባበቀች መሆኗን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ በጉባኤው ከ11 ሺህ ያላነሱ እንግዶች እንደሚጠበቁ አስታውቀዋል፡፡
ለጉባኤው የሚመጡ እንግዶች ስለ ኢትዮጵያ ጥልቅ መረጃን እንዲያገኙ የሀገርን ገጽታ የሚገነቡ ስፍራዎችንና የቱሪስት መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ ይደረጋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለጉባኤው በዓለም መድረክ ስሟን ከፍ አድርጎ የሚያስጠራ ዝግጅት ማድረጓንም አስታውቀዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025