የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

<p>ለጉባኤው የሚመጡ እንግዶችን ኢትዮጵያዊ እሴቶችን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ ዝግጅት አጠናቀናል-የቱሪዝም እና ሆቴል ማርኬት አሶሴሽን</p>

Feb 12, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦የአፍሪካ ህብረት ጉባኤን ለመታደም የሚመጡ እንግዶችን ኢትዮጵያ እሴቶች እና የቱሪስት መስህቦችን ለማስተዋወቅ ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የቱሪዝምና ሆቴል ማርኬት አሶሴሽን ገለፀ።

በመዲናዋ የተካሔደው የኮሪደር ልማት ለጉባኤው የሚመጡ እንግዶችን ምቹና ውብ በሆነ መንገድ ከማስተናገድ ባለፈ የንግድ እንቅስቃሴን ለማፋጠን እንደሚረዳቸውም ተገልጿል።

38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሁም 46ኛው የሥራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ የካቲት 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን እንግዶችን ለመቀበል ሁለንተናዊ ዝግጅት መጠናቀቁም ተጠቁሟል።


ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል አስጎብኝ ድርጅቶችና ሆቴሎች የህብረቱ ጉባኤን ለመካፈል ለሚመጡ እንግዶች ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቁመዋል።

የቱሪዝም እና ሆቴል ማርኬት አሶሴሽን የፕሮጀክት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አስማ መፍቱ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ አዲስ አበባ ውስጥ ሆቴሎች እንደየ ደረጃቸው እንግዶቻቸውን ለማስተናገድ ዝግጅት አጠናቀዋል።

በተለይም የኢትዮጵያን ባሕላዊ እሴቶች የሚያስተዋውቁ ምግቦች፣ አልባሳት፣ ባህላዊ እሴቶችና ሌሎች የቱሪስት መስህቦችን በፓኬጅ ደረጃ ቀርጾ ለማስተዋወቅ ዝግጅት መደረጉንም እንዲሁ።

ጉባኤው በአዲስ አበባ ውስጥ መካሔዱ በዋናነት የቱሪዝምና ሆቴል ዘርፉን ይበልጥ ለማስተዋወቅ ሰፊ እድል የሚፈጥር መሆኑንም ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

በመዲናዋ የተካሔደው የኮሪደር ልማት ለጉባኤው የሚመጡ እንግዶችን ምቹ በሆነ መንገድ ከማስተናገድ ባለፈ የንግድ እንቅስቃሴን ለማፋጠን እንደሚያግዝም ተገልጿል።

በዋናነትም በቅርቡ በመዲናዋ የተገነቡ መናፈሻዎችና ፓርኮችን ለማስጎብኝትም ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውም የእንግዶችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም የሚያስችሉ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.