ጋምቤላ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፦ የኮሪደር ልማት ከተሞችን በማዘመን ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የሚያደርግ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድ ገለፁ።
በጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
ርዕሰ መስተዳድሯ በልማቱ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ እንዳሉት የኮሪደር ልማት ከተሞችን በማዘመን ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው።
በተለይም የከተሞችን ገፅታ ከመቀየርና ለኑሮ ተስማሚ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥር ፕሮጀክት መሆኑንም ተናግረዋል።
የጋምቤላ ከተማ የኮሪደር ልማት የዲዛይንና የጥናት ስራው ባለፉት ሶስት ወራት ሲከናወን መቆየቱን ጠቅሰው፤ ዛሬ ወደ ትግበራ ምዕራፍ መሸጋገሩን ገልፀዋል።
በጋምቤላ ከተማ ለተጀመረው የኮሪደር ልማት ስኬታማነት የህዝቡ ሁለንተናዊ ድጋፍና ቀና ትብብር ሊጠናከር እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሯ አስገንዝበዋል።
የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ሳይመን ሙን(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት በክልሉ ርዕሰ በከተማ ጋምቤላ የሚከናወነው የኮርደር ልማት የከተማውን ማስተር ፕላን መሠረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም የእግረኛና የብስክሌት መንገድ፣ የአረንጓዴ መዝናኛ ቦታዎችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በማቀናጀት የሚተበገር ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል።
የጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ከ14 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው አራት ዋና ዋና መንገዶችን ለማልማትና ለማስዋብ ግብ ተጥሎ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀዋል።
በዚህም መሠረት ከአቦቦ ኬላ እስከ ባሮ ድልድይ፣ ከስላሴ እስከ ዶቦስኮ፣ ከአደባባይ እስከ ዲፖ እና ከአደባባይ ቄራ መስመር በመጀመሪያው ምዕራፍ የሚሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም በመጀመሪያው ምዕራፍ የሚከናወነው የኮሪደር ልማት ከ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እንደሚተገበር አብራርተዋል።
የኮሪደር ልማቱ ሲጠናቀቅ የጋምቤላ ከተማን ይበልጥ ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ከማድረግ ባለፉ ለኑሮ ምቹና ተስማሚ አካባቢን ለመፍጠር ያስችላል ሲሉም ከንቲባው አብራርተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025