የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>አፍሪካ ችግሮችን በመቋቋም ዕድገቷን እንድታፋጥን ዘላቂ የፋይናንስ ስርዓት መዘርጋት ይገባል - ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)</p>

Feb 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 05/2017(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ችግሮችን በመቋቋም ዕድገቷን እንድታፋጥን ዘላቂ የፋይናንስ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለጹ።

46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ "የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በስብሰባው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የአፍሪካ የወደፊት እጣ ፋንታ በጋራ ፈቃደኝነት እና ተግባር ላይ የተመሰረተ ነው ብለዋል።

መጪውን ጊዜ በስኬት ለመወጣት ትብብር ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ አፍሪካ ችግሮችን በመቋቋም ዕድገቷን ማፋጠን እንድትችልም ዘላቂ የፋይናንስ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የአፍሪካ ሕብረት 2063 አጀንዳን ለማሳካት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን በእጥፍ ማሳደግ እንደሚያስፈልግም እንዲሁ።

የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ስብሰባው ለመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችና ሌሎች ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.