የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>በምዕራብ ወለጋ ዞን ከ75 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለወረዳ ማዕከላት ደርሷል</p>

Feb 13, 2025

IDOPRESS

የካቲት 05/2017(ኢዜአ)፦ በምዕራብ ወለጋ ዞን 75 ሺህ 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለወረዳ ማዕከላት መድረሱን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በዞኑ የሕብረት ሥራ ማህበራት ጽህፈት ቤት የምርት ግብዓት አቅርቦት ቡድን መሪ አቶ ተስፋዬ ታሲሳ እንዳሉት በምርት ዘመኑ 251 ሺህ 340 ኩንታል አፈር ማዳበሪያ ለዞኑ አርሶአደሮች ይቀርባል።

ዘንድሮ የሚቀርበው የአፈር ማዳበሪያው ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 50 ሺህ ኩንታል ብልጫ እንዳለው ገልጸው፤ በእስከሁኑ ሂደትም 75 ሺህ 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በዞኑ በሚገኙ የወረዳ ማዕከላት መግባቱን አመልክተዋል፡፡


በቀሩት ጊዜያት የአፈር ማዳበሪያውን በማጓጓዝ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

የግብዓት አቅርቦትና ስርጭቱም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዞ የሚካሄድ በመሆኑ በፊት የነበሩትን አሰራር ችግሮች ከመቅረፍ ባለፈ አርሶ አደሩ ለእርሻ ልማት ስራው ማዳበሪያ በወቅቱ እንዲያገኝ እንደሚያስችል አስታውቀዋል፡፡

የዞኑ አርሶ አደሮች በአቅራቢያቸው በሚገኘው የማዳበሪያ ማሰራጫ ማዕከላት ተገኝተው በጊዜ መውሰድ እንዳለባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.