የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>በክልሉ የተተገበረው የምግብ ዋስትና ፕሮግራም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን ኑሮ እያሻሻለ ነው - ቢሮው</p>

Feb 13, 2025

IDOPRESS

ደሴ፤ የካቲት 5/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የተተገበረው የምግብ ዋስትና ፕሮግራም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን ኑሮ በማሻሻልና የከተሞችን ገጽታ በመቀየር አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ገለጸ።

በፕሮግራሙ በኮምቦልቻ ከተማ በከተማ ግብርና የተሰሩ የተለያዩ የልማት ተግባራት ዛሬ በባለድርሻ አካላት ተጎብኝተዋል።


በዚህ ወቅት የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሱለይማን እሸቱ እንዳመለከቱት፤ ባለፉት ሶስት ዓመታት በክልሉ ከ123 ሺህ የሚበልጡ ወገኖችን በፕሮግራሙ በማቀፍ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎችን በአካባቢ ልማት፣ ሥራ እድል ፈጠራና ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ በማሳተፍ ኑሯቸው እንዲሻሻል የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ተናገረዋል።

በከተሞችም ተጠቃሚዎችን በጽዳትና ውበት፣ በጎርፍ መከላከል፣ በተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ በመንገድ ሥራና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች በማሰማራት የከተሞች ገጽታ እንዲቀየር የሚያስችል ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

የፕሮግራም ተጠቃሚዎችም በሰሩት ልክ ከሚከፈላቸው ክፍያ በመቆጠብና በተመቻቸላቸው ተጨማሪ ብድር በመታገዝ በልዩ ልዩ ገቢ ማስገኛ ዘርፎች በመሰማራት ጥሪት ማፍራታቸውን ገልጸዋል።

በዚህ ዓመት ጥሪት ያፈሩ ወገኖችን በማስመረቅ በዘላቂነት ማቋቋም የሚያስችል ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተይዞ እየተሰራ መሆኑንጠቁመዋል።


የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምግብ ዋስትናና ሴፍቲኔት ፕሮግራም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ እታፈራሁ አሰግደው በበኩላቸው እንዳሉት፤ ተጠቃሚዎች ቀደም ሲል ጥቅም የማይሰጡና የቆሻሻ መጠያ የሆኑ ቦታዎችን በማልማት ላይ ይገኛሉ።

በተሰጣቸው ቦታ ላይም የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችን በማልማት ከራሳቸው ፍጆታ አልፈው ለአካባቢው ገበያ በማቅረብ ገበያ ማረጋጋት ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ተናግረዋል።


በኮምቦልቻ ከተማ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ከሆኑን ወስጥ አቶ አብዱራህማን አህመድ በሰጡት አስተያየት፤ መስራት የሚችል ጉልበት እያላቸው በገንዘብና በቦታ እጦት ተቸግረው እንደቆዩ አስታውሰዋል።

በፕሮግራሙ ከታቀፉ ወዲህ በተሰጣቸው የክህሎት ስልጠና በመጠቀም በከተማ ግብርና በመሰማራት የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ ጥሪት እያፈሩ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.