የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በአዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ማዕከል የተዘጋጀውን አውደ-ርዕይ ጎበኙ</p>

Feb 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፣ የካቲት 05/2017(ኢዜአ)፦ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በአዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ማዕከል የተዘጋጀውን ዐውደ-ርዕይ ጎብኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ሚኒስትሮች፣ የ46ኛው የአፍሪካ ኀብረት መደበኛ የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ተሳታፊ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች ዐውደ-ርዕዩን ጎብኝተዋል።

በዐውደ-ርዕዩ ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለብዝኅ ኢኮኖሚ ግንባታ በሰጠችው ትኩረት በግብርና፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን፣ ኢንዱስትሪ እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን መስክ የተመዘገቡ ስኬቶች ለዕይታ ቀርበዋል።

በተጨማሪም በግሉ ዘርፍ ግዙፍ ኩባንያዎች የቡና፣ አልባሳት፣ የጌጣጌጥ እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ውጤት አምራቾች አገልግሎቶቻቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.