አዲስ አበባ፤ የካቲት 05/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን ለመመስረት ሲካሄድ የነበረው የውይይት መድረክ ዛሬ በስምምነት ተጠናቋል።
የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን ለመመስረት የሚያስችል ጉዳዮች ላይ በሁለቱ ሀገራት የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ ሰፊ ውይይት ሲደረግ ቆይቷል።
በውይይቱም የሁለትዮሽ ረቂቅ የመመስረቻ ሰነድ ላይ የተለያዩ ግብዓቶችን በመጨመር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለፊርማ ዝግጁ እንዲሆን ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
ላለፉት ሁለት ቀናት የተደረገው ውይይት በጋራ ለመስራት በተስሟሟቸው አጀንዳዎች ዙሪያ በመፈራረም እና የጋራ መግለጫ በመስጠት መጠናቀቁን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያመረጃ ያሳያል።
በመድረኩ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የጅቡቲ መሰረተ-ልማት እና ኢኪዩፕመንት ሚኒስትር ሀሰን ሀሙድ፣ የጅቡቲ ንግድ እና ቱሪዝም ሚኒስትር መሀመድ ዋርሳማ እና ሌሎች የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025