ቡታጅራ፣ የካቲት 7/2017 (ኢዜአ)፡-የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን የሚገመግም መድረክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡታጅራ ከተማ መካሄድ ጀመረ።
"በጥራት ወደ ተሳለጠ የንግድ ስርዓት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ መድረክ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የንግድ ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በጉባኤው የሚኒስቴሩ የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የሚካሄድበት ሲሆን ለቀጣይ የሥራ አቅጣጫም እንደሚቀመጥ ተገልጿል።
በተጨማሪም የሁሉም ክልሎች የሴክተር ቢሮዎች የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ የሚገመገም ሲሆን የንግድ ተቋማት የሥራ እንቅስቃሴ ላይም ምልከታ ይደረጋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025