ወልድያ፤ የካቲት 8/2017 (ኢዜአ)፡- በሰሜን ወሎ ዞን በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ሰባት ሺህ የሚጠጉ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የዞኑ እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ተጠሪ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የሰሜን ወሎ ዞን የሌማት ቱሩፋት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በስታይሽ ከተማ ዛሬ ተካሂዷል።
የተጠሪ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ነጋ ጌታቸው፣ በውይይቱ ላይ እንዳሉት የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በስራ እድል ፈጠራ፣ በገበያ ማረጋጋትና የስራ ባህል በመቀየር አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።
በዚህም በዞኑ የሚገኙ ሰባት ሺህ የሚጠጉ ወጣቶችን በእንስሳት እርባታና ማድለብ፣ በንብ ማነብና በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስራ በማሳተፍ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ መደረጉን ገልጸዋል።
በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ስጋ፣ እንቁላልና አትክልትና ፍራፍሬ ለገበያ በማቅረብ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል።
በተጨማሪም በአሳ እርባታ የተሻሉ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመው በዘርፉ ወጣቶችን በአሳ ልማት በማሰማራት አሁን ላይ ለገበያ የአሳ ምርት ማቅረብ መጀመራቸውን ሀላፊው ጠቅሰዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት ንጋቱ፤ በዞኑ የሌማት ቱርፋት ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ወዲህ አበረታች ለውጦች እየተገኙ ነው።
ዘርፉ ከምግብ አቅርቦት ባለፈ የስራ እድል በመፍጠር የወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እያሳደገ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት የስራ እድል ከመፍጠር ባሻገር በምግብ ራስን ለመቻልና ህብረተሰቡ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኝ የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል።
የዛሬው ውይይትም በዘርፉ አፈጻጸም ላይ የታዩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም ማህበረሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መድረክ መሆኑን አስረድተዋል።
በውይይት መድረኩ ላይም የሰሜን ወሎ ዞን የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025