አዲስ አበባ፤ የካቲት 8/2017 (ኢዜአ)፡- የናይጀሪያው ኩባንያ ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ያለውን የሲሚንቶ የማምረት አቅሙን በዕጥፍ ለማሳደግ መዘጋጀቱን ገለፀ።
ኩባንያው በኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ ለመሰማራትም ፍላጎት እንዳለው አሳውቋል።
የዳንጎቴ ግሩፕ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አሊኮ ዳንጎቴ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ጋር በኩባንያው ኢንቨስትመንት ማሻሻያ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
አሊኮ ዳንጎቴ በማብራሪያቸው እንዳሉት የኢትዮጵያ መልክዓ ምድርና የአየር ሁኔታን ጨምሮ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችለየትኛውም የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሠማራት ምቹ ሀገር ናት።
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንታቸውን ለማስፋፋት አማራጮችን እየቃኙ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዛሬው ዕለትም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በኢንቨስትመንት ነክ ጉዳዮች መወያየታቸውን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ሪፎርም በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት የሚያነሳሳ እንደሆነም ጠቁመዋል።
ቀደም ብሎ በሲሚንቶ ኢንቨስመንት የተሰራማራው ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ምቹ የኢንቨስመንት ከባቢ በማየት ምርቱን በዕጥፍ ለማሳደግ መዘጋጀቱን አብስረዋል።
በዚህም በአመት 2 ነጥብ 5 ሚሊዬን ቶን ሲሚንቶ የማመረትን አቅም ወደ አምስት ሚሊዬን ቶን እንደሚያሳድገው አብራርተዋል።
ከሲሚንቶ ባሻገርም በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን በሚያሳድጉ ዘርፎች ለአብነትም በአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመክፈት እቅድ መያዙንም አንስተዋል።
በስኳር ልማት ያለውን ልምድ ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት በኦሞ ኩራዝ የማስፋፊያ ስራ እንደሚያከናውን ለአብነት ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል።
ለውጪ ሀገር አልሚዎች በተፈጠረው ልዩ ዕድል በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎታቸው እየጨመረ መምጣቱን ገልጸው፤ ዳንጎቴ ግሩፕ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025