አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2017(ኢዜአ)፡- ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅሞ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የውስጥ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ አስገነዘቡ።
በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ሶስቱ የሪጅዮ ፖሊስ ከተሞች 'ስማርት' ወደ ሆነ የገቢ አሰባሰብ እንዲገቡ ይደረጋል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
"ቃልን ወደ ባህል፤ ፀጋን ወደ ገቢ!" በሚል መሪ ቃል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ያዘጋጀው የታክስ ንቅናቄ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ክልሉ በዕቅድ ባስቀመጠው ልክ ገቢ መሰብሰብ ባለመቻሉ የበጀት ጉድለት ውስጥ ይገኛል ብለዋል።
ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅሞ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የውስጥ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በክልሉ አሁንም በመቀጠር ከሚገኝ ገቢ በስተቀር ከንግድ፣ ቤት ኪራይ፣ የገጠር መሬት መጠቀሚያ መሰል ዘርፎች የሚሰበሰበው ግብር አነስተኛ መሆኑን ጠቅሰው የገቢ ምንጩን ማስፋት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ተቋማዊ የማሻሻያ ስራ በመስራት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ሶስቱን የሪጅዮ ፖሊስ ከተሞች 'ስማርት' ወደ ሆነ የገቢ አሰባሰብ እንዲገቡ አንደሚደረግም አስታውቀዋል።
አመራሩና ባለሙያው ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ ለህዝብ የልማት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉም አክለዋል።
የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ አለማለቅ እና ደምወዝ በጊዜ መክፍል ያለመቻል ችግሮች ዋነኛ ምክንያት ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ አለመቻል መሆኑን በአጽንኦት ገልፀዋል።
ክልሉን የሰላም፣ የመቻቻልና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቁልፍ መሆኑን ገልፀዋል።
ለዚህም የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን በማዘመን እና የዲጂታል አሰራርን ተደራሽ በማድረግ የገቢ አሰባሰብ ስራን ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አለምነሽ ደመቀ በበኩላቸው፥ በክልሉ የገቢ አሰባሰብ ውጤታማነትን ለማሳደግና የፋይናንስ አቅም ለመፍጠር የተሰሩ ስራዎች አበረታች ቢሆኑም በርካታ ተግባራት እንደሚቀሩ ተናግረዋል፡፡
ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ቢሆንም የገቢ መሰረቱን በማስፋትና ግብይትን በደረሰኝ በመፈፀም በኩል ችግሮች እንዳሉም የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
ከአቅም በታች ገቢ መሰብሰብ፣ ውስን የማዘጋጃ ቤት ገቢ ላይ ትኩረት ማድረግ፣ የገቢ አሰባሰቡን በቴክኖሎጂ አለማዘመን፣ ማጭበርበርን እንደ ባህል የያዙና ከነጋዴ ጋር የሚተባበሩ ባለሙያዎች መኖር፣ የመንግስትና ፓርቲ መዋቅር የሚመሩ አካላት የገቢ አፈፃፀምን አለመደገፍና በዝርዝር አለመገምገም እንደ ችግር መነሳቱን ከክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በሌላ በኩል በክልሉ የተዘጋጀው የገጠር መሬት መጠቀሚያ አዋጅ እና የኢንቨስትመንት ግብር ላይ የተደረገው ማሻሻያ ተጨማሪ የገቢ አቅም እንደሚፈጥር በመድረኩ መገለጹም እንዲሁ።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025