መቱ፤ የካቲት 11/2017 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የጤና አገልግሎት አሰጣጡን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የማድረግ ስራዎች መጀመራቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ።
የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ቦኮና ጉታ እንደተናገሩት፥ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።
ከተጀመሩ ጥረቶች መካከል በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ከወረቀት ነጻ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል ብለዋል።
በዚህ ዓመትም በክልሉ በአስር ሆስፒታሎችና በአምስት ጤና ጣቢያዎች ከወረቀት ነጻ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ተደርጓል ነው ያሉት።
በቀጣይም በክልሉ በሁሉም የጤና ተቋማት ከወረቀት ነጻ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ከወረቀት ነጻ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ከተጀመረባቸው ተቋማት መካከል የመቱ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ካርል ሆስፒታል አንዱ ነው።
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሶላን በቀለ፤ በአሁኑ ወቅት በሆስፒታሉ እየተሰጠ የሚገኘው የሕክምና አገልግሎት ከወረቀት ነጻ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም ለተገልጋዩ የተቀላጠፈ የሕክምና አገልግሎት መስጠት እያስቻለ ሲሆን ከዚህ በፊት ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎችም መቀነሳቸውን ተናግረዋል።
የመቱ ሆስፒታል ከወረቀት ነጻ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን በጤና ሚኒስቴር አመራሮችና በክልሉ ጤና ቢሮ አመራሮች ተጎብኝቷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025