ወልዲያ፤ የካቲት 12/2017( ኢዜአ)፡-የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬና የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በወልዲያ ከተማ የተገነቡ የልማት ስራዎችን ዛሬ ጎብኝተዋል።
በወልዲያ ከተማ ከተጎበኙት የልማት ስራዎች መካከል 30 ሜትር ስፋት ያለው ዘጠኝ ኪሎ ሜትር የቀለበት መንገድ፣ የገበያ ማዕከልና ዲጂታል የሕዝብ ቤተ- መጻሕፍትና ሌሎች የልማት ስራዎች ይገኙበታል።
የቀለበት መንገዱ በከተማ አስተዳደሩ 750 ሚሊዮን ብር በጀት እየተከናወነ እንደሚገኝም ተመላክቷል።
በተመሳሳይም በከተማዋ በ16 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ ያለው ቤተ-መጻሕፍትም በስራ ኃላፊዎቹ ተጎብኝቷል።
የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ሰሞኑን በሰሜን ወሎ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸው ይታወሳል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025