የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>የክህሎት ልማት ዘርፉን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሪፎርም ዕቅዶች ተነድፈው ተግባራዊ እየተደረጉ ነው - የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር</p>

Feb 21, 2025

IDOPRESS

ሮቤ፤ የካቲት 13/2017(ኢዜአ)፡- የክህሎት ልማት ዘርፉን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሪፎርም ዕቅዶች ተነድፈው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአጋርፋ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ከ430 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያስገነባውን ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ህንጻዎች ለአገልግሎት አብቅቷል።


በምርቃ መርሃ ግብሩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝቷል።

ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ወቅት እንዳሉት በሀገር ደረጃ የክህሎት ልማት ዘርፉን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሪፎርም ዕቅዶች ተነድፈው ተግባራዊ እየተደረጉ ነው።

በአዲሱ ሪፎርም በየደረጃው የሚገኙ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የንድፈ ሀሳብና የተግባር ማዕከል እንዲሆኑ መሠረተ ልማት የማስፋፋት ስራው መጠናከሩን ገልጸዋል።


ኮሌጆቹ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን በማፍራት የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ መሠረተ ልማቶቹን መገንባት የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለውም አክለዋል።

ከዚህ አንፃር የአጋርፋ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ከ430 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በመመደብ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ህንፃዎች መገንባቱ የዚሁ ጥረት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።


የአጋርፋ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ዲን አቶ ፍራኦል ኢደኦ በበኩላቸው ኮሌጁ የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚውን ለማዘመን በግብርናው ዘርፍ የተማረ የሰው ኃይል ለማፍራት አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

በተጓዳኝ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ምርምሮችና የማህበረሰብ አገልግሎቶችን እያከናወነ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።

ኮሌጁ ያስገነባው ህንጻ የተማሪዎች የቅበላ አቅምን እንደሚያሳድግና የመማር ማስተማር ስራውን በውጤታማነት ለመተግበር አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል።

ህንጻዎቹ የተማሪዎች መኝታ፣ መማሪያ ህንፃ፣ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አደራሽና ሌሎች አገልግሎቶችን ያሟሉ በመሆናቸው ለማህበረሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ እንደሚያሳልጥም አመልክተዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው ኮሌጁ በቅርበት በመኖሩ በግብርና ግብዓትና የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎችን እንዲያገኙ እያገዛቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.