የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>ፀሃይ -2 አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራዋን በስኬት አጠናቀቀች</p>

Feb 21, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2017(ኢዜአ)፦በኢፌዴሪ አየር ኃይል ውስጥ የተሰራችው ፀሃይ - 2 የስልጠና አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራዋን በስኬት ማከናወን መቻሏን የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአቪየሽን ከባድ ጥገና ማዕከል ኮሎኔል መሰረት ጌታቸው ገልፀዋል።


ፀሃይ -2 አውሮፕላን ለበረራ ማሰልጠኛና ለሌሎች አገልግሎት መዋል የምትችል መሆኑን ያስታወቁት ኮሎኔል መሰረት ጌታቸው የተሰጣትን ግዳጅ በብቃት መፈፀም የሚያስችላትን የዘመኑን የአቭዬሽን ቴክኖሎጂ መታጠቋንም አብራርተዋል።

የአውሮፕላኗ ስኬታማ የሙከራ በረራ አየር ኃይሉ የደረሰበትን የከፍታ ጉዞ ጠቋሚ ነው ያሉት ምክትል አዛዡ በቀጣይነትም ወደ ምርት ሂደት ለመሸጋገር ፋብሪካውን የማደራጀት ፣የመፈተሻ እቃዎችን የማሟላትና የሙያተኞችን አቅም የማጎልበት ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡


የትራንስፖርት አውሮፕላን ስኳድሮን አዛዥ እና አብራሪ እንዲሁም የፀሃይ -2 የሙከራ በረራን በስኬት ያካሄዱት ሻለቃ ፍቃዱ ደምሴ በበኩላቸው አውሮፕላኗ አለም የደረሰበትን የአውሮፕላን ቴክኖሎጂ የታጠቀች የበረራ አቅሟም አስተማማኝ እና ተቋሙ ለያዘው የወደፊት ራዕይ ጉልህ አስተዋፅዖ የምታበረክት መሆኗን ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.