አክሱም፤የካቲት 13/2017 (ኢዜአ) ፡-ለግብርና ግብአት የመጋዘንና ሌሎች አገልግሎቶችን እንዲሰጥ በአክሱም ከተማ የተገነባው ሁለገብ ህንፃ ተመረቀ።
በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በ70 ሚሊዮን ብር የተገነባው ሁለገብ ህንፃ ለግብርና ግብአትና ለመሳሪያዎች መጋዘንና ሌሎችም አገልግሎቶች የሚውል መሆኑ ታውቋል።
በህንፃው ምረቃ ስነ ስርአት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ክፍሌ ወልደማሪያም፤ የተገነባው ባለ ሶስት ወለል ህንጻ ለግብርና ስራ የላቀ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
ህንፃው የግብርና መሳሪያዎችና የግብአት መጋዘን ያለው በመሆኑ ግብአቶችን ለአርሶ አደሮች በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ስለመሆኑ አንስተዋል።
መጋዘኑ በአንድ ጊዜ ከ60 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያና ሌሎችንም የግብርና ግብአቶች መያዝ የሚችል መሆኑንም ተናግረዋል።
በተለይም ለአክሱምና አድዋ፡ ሽሬና አካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች የግብርና ግብአቶችን በቅርበትና በአፋጣኝ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱም ከተማ ምክትል ከንቲባ አበበ ብርሃነ፤ የተገነባው ሁለገብ ህንፃ በተለይም ለአርሶ አደሮች አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል።
ኮርፖሬሽኑ በከተማው ለሚያከናውናቸው ስራዎች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉም አረጋግጠዋል።
ኮርፖሬሽኑ ከዚህ በፊት በውቅሮ ማራይ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገንብቶና የውስጥ ቁሳቁሶችንም አሟልቶ ማስረከቡ ይታወሳል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025