ጎንደር፤ የካቲት 13/2017(ኢዜአ)፡- የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በጎንደር ከተማ በፌዴራል መንግስት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የሠላም ሚኒስትሩ መሀመድ እድሪስ፣ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እና ሌሎችም የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በጉብኝታቸውም የጎንደር ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት እንዲፈታ ዳግም ግንባታው በመፋጠን ላይ የሚገኘውን የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ አድርገዋል።
በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃውን የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት የምሽት ድባብን እንዲሁም አለም አቀፍ ቅርስ የሆነውን የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት እድሳትና ጥገና ስራንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025